Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢፍጥር ፕሮግራም በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢፍጥር ፕሮግራም በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች የታደሙበት የኢፍጥር ፕሮግራም በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን የዝግጅቱ አስተባባሪዎች እና ታዳሚዎች እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቧል።
ኮሚሽኑ አያይዞም የኢድ አልፈጥር በዓል በሚከበርበት ወቅት የተለመደው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version