Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ወደ ፖርቶ ተዛወረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቼልሲ እና በማንቼስተር ሲቲ መካከል የሚካሄደው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ወደ ፖርቹጋል መዛወሩ ተገለጸ፡፡

በፍጻሜው ጨዋታ 12 ሺህ የሚደርሱ የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች ይታደማሉ ተብሏል፡፡

ቀደም ሲል ጨዋታው በቱርክ ኢስታንቡል አታቱርክ ኦሎምፒክ ስታዲየም እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር፡፡

አሁን ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ ፖርቹጋል ፖርቶ መዛወሩ ነው የተገለጸው፡፡

የሁለቱ የእንግሊዝ ቡድኖች የፍጻሜ ጨዋታ በመጪው ግንቦት 21 ቀን እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version