Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰባተኛው ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባዔ ዛሬ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።
“ምርምር ለዘላቂ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ጉባዔ 20 የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረጉባቸው ይጠበቃል።
የጉባዔው ዓላማ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምር በማድረግ የሀገሪቱን ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ለማገዝ መሆኑም ተገልጿል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ ከሀገሪቱ የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት የተውጣጡ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከባሌና አካባቢዋ የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።
‘ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version