Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 2 አሸነፈ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐይደር ሸረፋ ባስቆጠራቸው ሶስት ግቦች ነው ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ያረጋገጠውን ወልቂጤ ከተማን ያሸነፈ።

እስከ 89ኛው ዲቂቃ ላይ ሁለት አቻ በነበረው ጨዋታ ሀትሪክ የሰራው ሐይደር ሸረፋ በመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፏል።

የወልቂጤ ከተማን ሁለት ግቦች  አህመድ ሁሴን አስቆጥሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version