Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የህክምና ቱሪዝምን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህክምና ቱሪዝምን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ያለመ የውይይት ተካሄደ።
መርሃ ግብሩ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና በዋጋ ሜዲካል ሰርሺስ ትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
ለአይን ህክምናና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች ከጎረቤት ሃገር ሰዎች ገብተው አገልግሎት እንደሚያገኙ በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን ይህንን ማስቀጠልና ማስፋፋት ያስፈልጋል ተብሏል።
በዚህ ረገድ የግሉ የህክምና ዘርፍ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ኢትዮጵያ በባህል ህክምና ሰፋ ያለ እውቀት አላት ያሉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው÷ ዘርፉን ማስተዋወቅና መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
የባህል ህክምና ውጤቶች ፍቃድ ተሰጥቷቸው ሰዎች ወደ ሃገር መጥተው እንዲታከሙ፣ መድሃኒቶችንም ወደ ውጭ መላክ የሚቻልበት ሁኔታ ለማመቻቸት ይሠራልም ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የህክምና ቱሪዝም ያለው ጠቀሜታን በተመለከተም ጥናት መቅረቡን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

 

Exit mobile version