Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ ብለው የሚያስተላልፉት ድምጽ ፍጹም ሀሰት ነው- ብልጽግና ፓርቲ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፓርቲው ሀሰተኛ መረጃን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሚታወቁ ሚዲያዎች በቅርቡ ከተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ ብለው የሚያስተላልፉት ድምጽ ፍጹም ሀሰት የሆነ፣ ከስብሰባው የተወሰደ አንድም ቃል የሌለው፣ የፓርቲያችን ፕሬዚዳንት በተለያዩ ጊዜያት ካደረጓቸው ንግግሮች የተወሰዱ ቃላትን በመገጣጠም የተቀነባበረ ሀሰተኛ ድምጽ ነው ነው ብሏል ፓርቲው።

የኢትዮጵያን እድገትና ብልጽግና የማይፈልጉ የውስጥና የውጭ ሃይሎች ገና ከዚህ በላይ የሀሰት ወሬዎችን ሊፈበርኩ ይችላሉ በመግለጫው ጠቅሷል።

የኢትዮጵያን ብልጽግና ማስቆም አይደለም ማዘግየት የሚችል አንድም ሃይል አይኖርም።

ህዝባችን ከዚህ አይነት ሀሰተኛ የመረጃ ምንጮች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብሏል ፓርቲው።

ምንጭ፦ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version