Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን በመስኖ የለማ ስንዴ ማሳንና በባሌ ሮቤ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በመስኖ የለማ ስንዴ ማሳንና በባሌ ሮቤ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ፡፡
የመስኖ ስንዴው በቴክኖሎጂ የታገዘና በባለሀብቶች እየለማ መሆኑ ታውቋል፡፡
በተያያዘ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ሮቤ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝት የተደረገባቸው የልማት ስራዎች የባሌ ጎባ አስተዳደር ካከናወናቸው የልማት ስራዎች ውስጥ በኢትዮ ኤምሬት እና በአስተዳደሩ በጋራ የተገነባ ሆስቲታል እንዲሁም ዋቆ ቡቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በፈትያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version