Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 የትምህርት ዘመን ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 23-25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ በ5 ሺህ 520 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 420 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
ፈተናውን ለመስጠትም የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኃላፊው መምህራንና ወላጆች በቀሪ ጊዜያት ለተማሪዎች ስነልቦና ድጋፍ ሊያደርጉላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የትምህርት ቤት አመራሮች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version