Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቢሾፍቱ ከተማ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ 63 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ 63 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፣ጤና ጣቢያ፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ የአረጋውያን ማዕከል፣ ትምህርት ቤቶች ፣ የስፖርት ማዕከል እና መንገዶች ይገኙበታል።
በ98 ሚሊየን ብር ወጪ እየተሰሩ ከሚገኙ አራት የውሃ ፕሮጀክቶች መካከል ዛሬ ሁለቱ የተመረቁ ሲሆን 10 ሺህ የከተማው እና የገጠር ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።
በዚህም የከተማውን የውሃ ተደራሽነት ከነበረበት 90 በመቶ ወደ 92 በመቶ ከፍ ያደርገዋል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም በ ሲ እና ኢ ወንድማማቾች የብረት ፋብሪካ በ15 ሚሊየን ብር ወጪ ቃጅማ እና ዲባዩ ቀበሌ መካከለኛ ጤና ጣቢያ ተመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ ቦሪሶን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version