Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምዕራብ አርሲ ለ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ምርጫ ቦርድ ማስተባበሪያ አስታወቀ።
የዞኑ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በቀለ በዞኑ 11 የምርጫ ክልሎች እንደሚገኙ ተናግረዋል።
እስካሁንም ለ7 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት የተከናወነ ሲሆን የ4 ምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ነገ ይካሄዳል ብለዋል።
በዞኑ 961 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን ለ3 ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና ወስደዋል።
ምርጫው የኮቪድ ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ ለማካሄድም ሁለት ሁለት ሰዎች በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያዎች ተመድቡኣል።
በዞኑ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች በምርጫው ድምጽ ለመስጠት ተመዝገባዋል።
የሻሸመኔ ከተማ የምርጫ አስተባባሪ አቶ አማረ ሙልዬ በበኩላቸው ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ ሙሉ በሙሉ መድረሱን ጠቁመው ስርጭቱ ግን አልተጀመረም ብለዋል።
በከተማው ስር 3 የምርጫ ክልልና 126 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ።
በምስክር ስናፍቅና ጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version