Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አጋሮ ከምርጫ በኋላ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመለሰች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አጋሮ ከተማ ከምርጫ በኋላ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሳለች።

ትላንት በምርጫ ምክንያት በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ተቋማት ተዘግተው የነበረ ሲሆን፥ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጦ ነበር።

በዛሬው ዕለት በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን፥ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት ተመልክቷል።

በሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version