Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ኢትዮጵያ ጥቅሟን ያስጠበቀችበት እና አዳዲስ ግንኙነቶችን ያጠናከረችበት ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ ዳቮስ የተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ኢትዮጵያ ጥቅሟን ያስጠበቀችበት እና አዳዲስ ግንኙነቶችን ያጠናከረችበት ነው ተባለ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የልዑካን ቡድን በዳቮሱ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አጠናቋል።

ፎረሙ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የገነባቻቸው የሁለትዮሽ እና ሁለንተናዊ ግንኙነቶች ያደሰችበት እና አዳዲስ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን መጀመር የቻለችበት መሆኑም ተጠቅሷል።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ረዳት እና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብይ ኤፍሬም ለጣቢያችን እንደተናገሩት፥ በፎረሙ ላይ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ትስስር መፍጠር ተችሏል።

በተለይም ኢትዮጵያ በዓለም፣ በአፍሪካ ብሎም በቀጠናው ሀገራት በኢኮኖሚው አውድ ውስጥ ባላት ድርሻ እና ሚና ለኢኮኖሚ አጋርነት እና ትስስር የምትመረጥ ሀገር መሆኗ የታየበት መድረክ እንደሆነም ተናግረዋል።

ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለመተግበር የጀመረችው ቁርጠኝነትም፥ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ተፈላጊነት ከፍ ያደረገ እንደነበርም አንስተዋል።

Exit mobile version