Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሰበታ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰበታ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ ስምንት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በፍጥነት ከጀሞ ወደ አለምገና ሲጓዝ ፉሪ የሚባል ቦታ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከሰበታ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version