Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶ/ር አብረሃም በላይ የወንጪ -ደንዲ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር አብረሃም በላይ የገበታ የወንጪ -ደንዲ  የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

ዶክተር አብረሃም  በላይ በጉብኝቱ ወቅትም÷ ከ3 ወራት በፊት የተጀመረው የፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ከክረምት በፊትና በክረምት ወራት መሰራት ያለባቸው ስራዎች በእቅድ ተለይተው በመተግበር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት እና የወሰን ማስከበር ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በፕሮጀክቱ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ለመሰማራት ባለሀብቶች ፕሮፖዛል እያቀረቡ መሆኑን ዶክተር አብርሀም ተናግረዋል።

አያይዘውም አሁንም ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር አብረሃም በላይ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው  የወንጪ -ደንዲ ፕሮጀክት አስተባባሪ  መሆናቸው ይታወቃል።

በዙፋን ካሳሁን

ፎቶ ከኢዜአ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version