Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም ባንክ ለደቡብ ሱዳን የ113 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

AGOK, SOUTH SUDAN - MARCH 2012: A scene in Abathok village during an International Committee of the Red Cross distribution of seeds, agricultural tools and food staples to households in villages around Agok, South Sudan. Approximately 15,000 people displaced by fighting in May 2011 were given sesame, groundnuts and sorghum seed, plus tools for tilling and some food as seed protection. (Photo by Tom Stoddart/Getty Images)

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለደቡብ ሱዳን የ113 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ በደቡብ ሱዳን ያለውን የምግብ እጥረት ለማቃለል ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ለመደገፍ የሚውል መሆኑም ነው የተገለጸው።
የዓለም ባንኩ በትላንትናው ዕለት ያበረከተውን የ 113 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ደቡብ ሱዳን ተረክባለች።
የደቡብ ሱዳን የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስትሩ ጆሴፊን ጆሴፍ ላጉ ÷ የኑሮ ልማት ፕሮጀክት እና የአስቸኳይ ጊዜ አንበጣ ምላሽ ፕሮጀክት ስር የተገኘው ድጋፍ አርሶ አደሮችን በብቃት እርሻዎቻቸውን በአግባቡ የማስተዳደር አቅምን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ምርቶቻቸውን ለማሻሻል አዲስ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ ያስችላል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ አያይዘውም ሁለቱ ፕሮጀክቶች የተቀረፁት የገጠር ኑሮን ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ፣ የግብርና ምርትን ለማሳደግ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለማስቆም አስተዋፅኦ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት።
በደቡብ ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው÷ ፕሮጀክቶቹ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ቤተሰቦች ምግብ እና ሌሎች ምርቶችን ለማምረት ያስችላቸዋል ፡፡
አያይዘውም ደቡብ ሱዳናውያን በቂ ምርት ማምረት መቻል አለባቸውም ነው ያሉት።
የፕሮጀክቶቹ ስኬታማ አፈፃፀም ለደቡብ ሱዳን የልማት አጋሮች እንዲሁም ለሀገሪቱ ተጨማሪ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡
እንደተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ 7 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ከሀገሪቱ 60 በመቶ ደቡብ ሱዳናውያን በዚህ አመት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ያሳያል።
ከነዚህም ውስጥ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ወደ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚጠጉ ሕፃናት ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል።
ምንጭ፡- ሲጂቲኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
See Translation
May be an image of 1 person and outdoors
180
4 Comments
2 Shares
Like
Comment
Share
Exit mobile version