Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የድንቅነሽ ቅጂ በዩኔስኮ ጽ/ቤት በቋሚነት ለዕይታ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅጂ በዩኔስኮ ጽህፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ እንዲቀርብ ማበርከቷን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ አስታውቀዋል፡፡
በድርጅቱ ፅህፈት ቤት የምትቀርብበት ሥነ-ስርዓትም ተካሂዷል፡፡
አምባሳደር ሄኖክ ኢትዮጵያ የድንቅነሽን ቅጂ ለዩኔስኮ በማበርከቷ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ድንቅነሽ ዘር፣ ጎሳና ሀይማኖት ሳንለይ የጋራ ሰብአዊነታችን መገለጫ ናት ብለዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የተቀረፀ ንግግር በስነ ስርዓቱ ላይ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት እንደሆነች ተንፀባርቋል።
በመርሃ ግብሩ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሬ አዙሌ፣ የሉሲን ቅሪተ አካል ያገኘው ቡድን አባላት ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን እና ኢቭ ኮፐንስ እንዲሁም የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች መገኘታቸውን ከአምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version