Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በክልሉ በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ፡፡
በዚህም ርዕሰ መስተዳድሩ የሐዋሳ አዳሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ ስራን እንዲሁም የሶሬሳ ጉዱማሌ ህንፃ ግንባታ ስራን ተመልክተዋል፡፡
የተጎበኙት የልማት ስራዎች በክልሉ በግንባታ ላይ ያሉና በድምሩ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጁ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡
አቶ ደስታ ሌዳሞ የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም ጥንካሬና ጉድለት በመለየት በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አመራር ለመስጠት ያለመ ጉብኝት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እንደ ሀገር የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ የማስገባት ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version