Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሰላም ተመላሾችን ከማኀበረሰቡ ጋር የማቀራረብና የዕርቀ ሰላም ስራ እየተሠራ ነው- የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመተከል ዞን የሰላም ተመላሾችን ከማኀበረሰቡ ጋር የማቀራረብና የዕርቀ ሰላም ስራ እየተሠራመሆኑን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ገለፁ።
ኮማንድ ፖስቱ የሰላም አማራጩን ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ማዕከል የገቡ ከ 1ሺህ 600 በላይ ታጣቂዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል።
በዞኑ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም ሞትና መፈናቀልን ለማስቀረትና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ኮማንድ ፖስት ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የተሠሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በዞኑ በፀጥታ ችግር ምክንያት አንድም ሰው ሊሞት አይገባውም፤ ታጣቂዎች የሠላምና የልማት ኃይል መሆን ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
የቤኒንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የክልሉ መንግስት ታጣቂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረው በቀጣይም የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ያሉ ሲሆን ÷ሰልጣኞቹም የበደልነውን ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን የልማት ኃይል ሆነን እንክሳለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version