Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪምየር ሊጉ ሰበታ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።

ሰበታ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ሰበታ ከተማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሰበታ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ገብረማርያም እና አዲስ ተስፋዬ ሲያስቆጥሩ፥የሃዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ መስፍን ታፈሰ አስቆጥሯል።

እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታን ሶዶ ከተማ ላይ ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የወላይታ ድቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቸርነት ጉግሳ 75 ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ጅማ አባ ጅፋር እና ስሑል ሽረ በትግራይ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

Exit mobile version