Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝና ጣሊያን ለፍጻሜ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ማምሻ በተደረገ ጨዋታ እንግሊዝ ዴንማርክን በማሸነፍ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ማለፏን አረጋገጠች፡፡
ጨዋታው በመደበኛ ሰዓት በአንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን በተጨመረ 30 ደቂቃ እንግሊዝ አንድ ጎል በማከል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
በዚህም ለአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ መድረሷን ያረጋጋጠች ሲሆን፤ ለፍጻሜው ጨዋታ ከትናንት በስቲያ ጣሊያን ስፔንን ማሸነፏል ተከትሎ እንግሊዝና ጣሊያን ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡
የፍፃሜ ጨዋታውም እሁድ ከምሽቱ 4 ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version