Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

60 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)60 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያመመለሳቸው ተገለጸ።
በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በሊባኖስ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ጊዜያዊ መጠለያ ተጠልለው ከሚገኙ ዜጎች መካከል 60 ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ባልደረቦች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version