Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለሃብቶች ለመከላከያ ሰራዊት ያሰባሰቡትን ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከቡ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ድጋፍ ከባለሃብቶች ተረክቧል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ መስዕዋትነት እየከፈለ ለሀገር ህልውና ለሚዋደቀው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን 2 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ቃል ገብቶ ነበር።
በዚሁ መሰረት ባለሃበቶች ያሰባሰቡትን ድጋፍ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ተረክበዋል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ኤም ደብሊው ኤስ (MWS) እና ሆራ ትሬዲንግ እያንዳንዳቸው 10 ሚሊየን ብር ለመከላከያ፣ 5 ሚሊየን ብር ደግሞ ለተቸገሩ ወገኖች ምገባ የሚውል ድጋፍ አስረክበዋል።
ወይዘሮ አዳነች ህዝቡ እና ባለሃብቱ የመከላከያ ደጀንነቱን በሚገባ ማስመስከር እንደሚጠበቅበት በመግለጽ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅበዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ከከተማዋ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ያሰባሰበውን 2 ቢሊየን ብር ለመሀገር መከላከያ ሰራዊት ማስረከቡ ይታወሳል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version