Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት ያካሄዳል፡፡
የምክር ቤቱ የፕሬስ እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው ጉዳዩን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም ምክር ቤቱ ነገ ሃምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለአንደ ቀን በሚያካሂደው 8ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎችን አብራርተዋል::
በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ በሚያካሂደው ጉባኤ የበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአስተዳደሩ የኦዲት ዘገባ ሪፖርትም ለምክር ቤት እንደሚቅርብና ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ሃላፊው መግለጻቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የ2014 በጀትን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version