Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ አፍሪካ የተከሰተው አለመረጋጋት የታቀደና ዴሞክራሲ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው – ሲሪል ራማፎሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ አፍሪካ የተከሰተው አለመረጋጋት ቀደም ተብሎ የታቀደ እና ዴሞክራሲን ለማኮሰስ የተፈፀመ ነው ሱሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ገለጹ።

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ መታሰራቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ በተነሳው አለመረጋጋት የ212 ሰዎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ ነው።

በሁከቱ ከጠፋው የሰው ህይወት በተጨማሪ 800 ያህል ሱቆች እንደተዘረፉና በአጠቃላይ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ንብረትም መዘረፉን የኩዋዙሉ ናታል ግዛት ከንቲባ ተናግረዋል።

ራማፎሳ ብጥብጡን ተከትሎ የዙማ መኖሪያ መንደር የሚገኝበትን ኩዋዙሉ ናታል በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት÷ እነዚህ ሁሉ መጠነ ሰፊ ዘረፋዎች አስቀድሞ በተደራጀ ቡድን ታቅደው የተፈፀሙ ናቸው ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸውም የተፈፀመው ስርዓት አልበኝነትና ዝርፊያ በሀገሪቷ እያደገ ያለውን ዴሞክራሲ ለማኮሰስ እንደሆነ አመላክተዋል። በቀጣይም ወንጀል ፈፃሚዎችን ለይቶ ለፍርድ የማቅረብ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version