Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ኬንያ ጅቡቲን ረታች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረገ የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ኬንያ ጅቡቲን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸንፍ በውድድሩ የመጀመሪያዋ ሶስት ነጥብ ያገኘች አገር ሆናለች፡፡
በትናንትናው እለት የተጀመረው ውድድር እስካሁን ሶሰት ጫዋታዎችን ያሰተናገደ ሲሆን÷ ሁለቱ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አንዱ ደግሞ በመሸናነፍ ተጠናቋል፡፡
በዚህም መሰረት በመክፈቻው ዕለት ኢትዮጵያና ኤርትራ 3 ለ 3 ሲለያዩ በዛሬው መርሐ-ግብር የመጀመያው ጨዋታ ኡጋንዳና ኮንጎም ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት 90 ደቂቃውን አጠናቀዋል፡፡
የዛሬው ሁለተኛ መርሐ-ግብር ኬንያንና ጅቡቲን ያገናኘ ሲሆን ኬንያ  ባስቆጠረቻቸው 3 ጎሎች ሶስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች፡፡
በፌቨን ቢሻው
ፎቶ፡-የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version