Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቶኪዮ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በመክፈቻ መርሃ ግብሩም ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራትን የወከሉ ልዑካን የሃገራቸውን ሰንደቅ አላማ በመያዝ በታዳሚያን ፊት አልፈዋል፡፡
በዘንድሮው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከ205 ሀገራት የተውጣጡ ከ11 ሺህ በላይ የኦሊምፒክ አትሌቶች በ33 አይነት ስፖርቶች ይሳተፋሉ፡፡
በውድድሩ ለአሸናፊዎች 5 ሺህ የተለያዩ ሜዳሊያዎች የተዘጋጁ ሲሆን፥ ሜዳሊያዎቹ ጥቅም ላይ ከዋሉ መገልገያ ቁሳቁሶች ተዘጋጅተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በኦሊምፒኩ በአትሌቲክስ፣ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት እና ቴኳንዶ ትሳተፋለች፡፡
በተለይም በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያ የሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ እንደምትገባም ይጠበቃል፡፡
በአራት ዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው ኦሎምፒኩ ባለፈው ዓመት መካሄድ ቢኖርበትም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለአንድ አመት መራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version