Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራን በባለስቲክ ሚሳኤሎች ፋንታ ሳተላይት ለማምጠቅ መዘጋጀቷን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን በባለስቲክ ሚሳኤሎች ፋንታ ሳተላይት ለማምጠቅ ቦታ ማዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡

የሃገሪቱ የመረጃና ኮሙኒኬሽን  ቴክኖሎጂ ሚኒስትር መሀመድ ጃቫድ ዛሪ ዛፋር ሳተላይትን ወደ ምህዋር ለመላክ አንድ ጣቢያ እየተዘጋጀ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

አክለውም ይህ ከተጠናቀቀ በኋላ  ተጨማሪ አምስት ሚሳኤሎችን ለማስጀመር  ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልፀዋል፡፡

ኢራን ከዚህ ቀደም ለሁለት ጊዜያት ሚሳኤሎችን ለማምጠቅ ጥረት አድርጋ ሳይሳካላት እንደቀረ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ኢራን ሳተላይቱን ምህዋር ላይ ለማሳረፍ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ባለስቲክ ቴክኖሎጂን ልትጠቀም ትችላለች ስትል ስጋቷን እየገለፀች ይገኛል፡፡

ለባቲስቲክ ሚሳይል ልማት ሽፋን  ነው ያለው አሜሪካ በተጨማሪም ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሊውል ይችላል ብላለች፡፡

ኢራን በበኩልዋ ይህን  የአሜሪካን ውንጀላ  አስተባብላለች፡፡

ኢራን የአብዮታዊ ዘብ አዛዥ   በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መገደሉን ተከትሎ በፈረንጆቹ 2015 የኒውክሌር ስምምነት ላይ የተጣለውን ማንኛውንም እገዳ እንደማታከብር አስታውቃ ነበር፡፡

እንዲሁም ኒውክሌር መጠን ላይ ቅነሳ እንደማታደርግና ኒውክሌርን ለምርምርና ልማት መጠቀሟን እንደምትቀጥል ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

Exit mobile version