Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ያለ ምንም የጸጥታ ችግር መከበሩን የፌደራል ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት የተከበረው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ያለ ምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ምስራቅ ዳይሬክተር ኮማንደር ጌትነት ዋሴ እንደገለጹት ÷ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፌደራል ፖሊስ፣ የምስራቅ ሀረርጌ፣ የሐረሪ ከልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከሀገር መከላከያ እና ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት እንዲሁም ከቤተክርስቲያኗ አባቶች ጋር በቅንጅት ተሰርቷል፡፡
በዓሉን ለማክበር በመጡ ምዕመናን ላይ አንዳንድ የስርቆት ወንጀል በፈፀሙ አካላት ላይ በተቋቋመው ፈጣን የፍርድ ችሎት አማካኝነት ከአንድ ዓመት እሰከ ሁለት ዓመት የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version