Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአልጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ለሚኒስትሩ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
 
ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
በተጨማሪም ሚኒስትሩ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version