Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደብረ ብርሃን፣ ቦንጋ እና ሃራምቤ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ23 ፕሮግራሞች በመደበኛ፣ በማታ እና በክረምት 231 ተማሪዎችን በ2ኛ ድግሪ፣1 በ3ኛ ድግሪ በታሪክና ቅርስ አስተዳደር አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲም ለሁለተኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 821 ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ ተመራቂዎች አስቸጋሪውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመከላከልና ተፅእኖውን በመቋቋም ለዛሬው ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

የሃራምቤ ዩኒቨርስቲም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 683 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ÷ የግል ትምህርት ተቋማት አስተምሮ ከማስመረቅ ባለፈ ክልሉ ላለው የትምህርት ልማት አጋዥ እየሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡

በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ ትምህርት ቤቶች የሚደረገው የቁሳቁስና የግብዓት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኤርሚያስ በጋሻው እና አይናለም ስለሺ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version