Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሀገርን ዳር ድንበርና ህልውና ለማስጠበቅ እስከ ህይወት መስዋዕትነት እንከፍላለን- የጉራጌ ዞን ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ዳር ድንበርና ህልውና ለማስጠበቅ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን የጉራጌ ዞን ወጣቶች ገለጹ፡፡
በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ መከላከያ ሰራዊት ለመቀላቀል ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሸኙ የዞኑ ወጣቶች ÷ እኛ እያለን የሀገርን ዳር ድንበርና ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል መሞከር የማይቻልና የማይሳካ ህልም ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ችግር በገጠማት ጊዜ ወጣቱ ቀድሞ በመሰለፍ ከአያት ቅድመ አያቶቹ የተረከባትን ሀገር ሳያስደፍር ማስቀጠል ይጠበቅበታል ያሉት ወጣቶቹ÷ ሰርቶ ማደግና መለወጥ የሚኖረው ሀገር ስትኖር መሆኑንም አውስተዋል፡፡
በመሆኑም አሁን ላይ ኢትዮጵያ የገጠማትን የውስጥና የውጭ እንዲሁም የጁንታው ርዝራዦች ኢትዮጵያን ለማፍረስና ዳር ድንበርን ለማስደፈር እያደረጉት ያለውን ጥረት ለማክሸፍ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን ተካ÷ የዞኑ ማህበረሰብ ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
በዞኑ ለ2ተኛ ዙር ወደ መከላከያ ሰራዊቱ ለመቀላቀል የተመለመሉ በርካታ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል ሽኝት መደረጉን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelev
Exit mobile version