Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሁሉም ዜጋ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ሊደግፍ እንደሚገባ ለሠራዊቱ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተቋቋመው የሀብት አሰባሳቢ ብሔራዊ ኮሚቴ ጥሪ አቅርቧል።
ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል 6800 የአጭር ጽሁፍ መልእክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥርም ይፋ ተደርጓል።
ይፋ በተደረገው ቁጥር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚችለውን የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችል ኮሚቴው ገልጿል።
የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ እና የንግድ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በጋራ በሰጡት መግለጫ መከላከያ ሠራዊቱን መደገፍ የሀገርን ሕልውናን ማረጋገጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት አጣብቂኝ ውስጥ እንደመሆኗ ዜጎች በሚችሉት ሁሉ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version