Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ 176 በላይ ተማሪዎቹን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ3 ሺህ 176 በላይ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በተጨማሪም የዩኒቨርስቲው የትምህርት ሴኔት ለ5 ምሁራን የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱ ነው የተገለጸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሐብታሙ አበበ ÷ ዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር ፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ጥራትን፣ ፍትሐዊነትን፣ ተደራሽነትንና አግባብነትን ለማረጋገጥ መስራቱን አንስተዋል።

ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተማሪዎቹም ሀገራቸውን እንዲወዱና የሰላም ዘብ ሆነው እንዲቆሙ አሳስበዋል፡፡

ቀጣይ የስራ ዘመናቸው መልካም እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በነገው እለት በዱራሜ ካምፓስ 434 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅም ለማወቅ ተችሏል።

በፕሮግራሙ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ማኒስቴር ሚንስትር ደኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎቹ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳታፊ በመሆን ችግን ተክለዋል፡፡

በሰላማዊት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version