Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመዲናዋን የውሃ ስርጭት ለማሻሻል እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የመዲናዋን የውሃ ስርጭት ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት 5 ኪሎ ሜትር ከፍተኛ እና ከ60 ኪሎ ሜትር በላይ መለስተኛ የውሃ መስመር ዝርጋታ ማከናወኑንም አስታውቋል።

የውሃ መስመር ዝርጋታው በከፍተኛ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ መስመር በመከፋፈል የተከናወነ መሆኑንም ገልጿል።

ከፍተኛው በዋናው መስሪያ ቤት እና ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት፥ መካከለኛ እና አነስተኛ መስመሮች ደግሞ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አማኝነት የተዘረጉ ናቸው ተብሏል።

የውሃ መስመሮቹ የመንገድ ግንባታ በሚከናወንባቸው፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና አዳዲስ ወደ ስርጭት የሚገቡ የውሃ ፕሮጀክቶችን ታሳቢ በማድረግ መዘርጋታቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version