Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት በነፋስ መውጫ ከተማ የግለሰብና የማህበራዊ ተቋማት ንብረቶችን አውድሟል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት በደቡብ ጎንደር ዞን ነፋስ መውጫ ከተማ የግለሰብና የማህበራዊ ተቋማት ንብረቶችን ዘርፎ የተረፈውን ደግሞ አውድሟል።
በከተማዋ የነፋስ መውጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ÷ ባንኮችን፣ የመብራት ማከፋፈያ ጣቢያ፣ ትምህርት ቤቶችን እንዲሁም የመንግስት ተቋማትንና መሰረተ ልማቶችን መዝረፉ ነው የተገለፀው፡፡
ሆስፒታሉ በአመት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን÷ አሁን ላይ ንብረቶቹ በሙሉ በመዘረፋቸውና በመውደማቸው ድንገተኛ ህክምና እንኳን መስጠት አለመቻሉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ብርሀኑ ሙሉ አስረድተዋል፡፡
በጦርነት ታሪክ የህክምና ተቋማትን ማፍረስ አለም አቀፍ ስምምነቶችን የጣሰ መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የህክምና ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በሆስፒታሉ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችንና ማሽኖችን በመዝረፍ የወሰደ ሲሆን÷ መውሰድ ያልቻላቸዉን የኤክስሬይና የላብራቶሪ ማሽኖችን ባሉበት አውድሟቸው ሸሽቷል ብለዋል።
በዙፋን ካሳሁን እና ምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version