Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ700 በላይ አምቡላንሶች ለክልል እና ከተማ አስተዳደሮች ተሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ከ700 በላይ አምቡላንሶችን ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች አስረከበ።

አምቡላንሶቹ የእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ እና የህሙማን ቅብብሎሽን ለማሻሻል ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር ላቀው አምቡላንሶች ለታለመላቸው አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ አመራሮች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የሚደረገው የአምቡላንስ ድጋፍ እንደሚቀጥል ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version