Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሉዛን ዳይመንድ ሊግ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በሉዛን ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በውድድሩ በ1 ሺህ 500 ሜትር የተሳተፈችው አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን ስታጠናቅቅ አትሌት ሂሩት መሸሻ በ6ኛነት ውድድሯን ጨርሳለች።
በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ውድድር ደግሞ በሪሁ አረጋዊ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቋል፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ 5ኛ እንዲሁም ሙክታር ኢድሪስ 6ኛ በመሆን ውድድሩን ሲያጠናቅቁ ጌትነት ዋለ ውድድሩን ማቋረጡን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version