Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለሚገኙ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ 450 ወገኖች ማዕድ አጋሩ፡፡
ቢሮው የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብርን ምክንያት በማድረግ ነው በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ ያጋራው፡፡
“መልካም ማድረግ እና ለሌሎች ማካፈል “በሚል በተካሄደው የማዕድ ማካፈል መርሃ ግብር ላይ የቢሮው ሃላፊ ዶክተር መስከረም ዘውዴ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
Exit mobile version