Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩ የደሴ ልጆች እና ወዳጆች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳና አውሮፓ የሚገኙ የደሴ ልጆች እና ወዳጆች በ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጪ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉ በውጭ ሀገር ነዋሪ በሆኑት አቶ ሽመልስ መኮንን እና ሰለሀዲን እሸቱ አስተባባሪነት የተሰበሰበ ሲሆን÷ ዓይነቱም ምግብ፣ አልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተደረገው ድጋፍም በሁሉም ትምህርት ተቋማት ተጠልለው  ለሚገኙ ከአማራ እና አፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ይውላልም ነው የተባለው፡፡

ድጋፉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት አቶ ብርሀኑ አሰፋ እና ወይዘሮ ሳባ ገብረሥላሴ ለከተማዋ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል አስረክበዋል።

በሰብለ ሲሳይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version