Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጀርመን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ኑረንበርግ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
በኑረንበርግ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር አስተባባሪነት በተዘጋጀው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን መሳተፋቸው ተገልጿል።
በመርሃግብሩ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚሆን 1 ሚሊየን 88 ሺህ ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
የኮሚዩኒቲ አባላቱ በቀን አንድ ዩሮ ለወገን በማዋጣት ያለማቋረጥ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል ነው የተባለው።
አባላቱ ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ ለሀገር ጥሪ ሲደረግና በራሳቸው ተነሣሽነት የመንግሥትን ሀገር የማዳን ጥሪ በመደገፍ፣ ለኢትዮጵያ አለኝታነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version