Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ህወሓት እንጂ ሀገር አትፈርስም- ዘማቹ ረ/ፕሮፌሰር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕልውና ዘመቻ ጥሪውን ተቀብለው በግንባር የሚገኙት ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው “እኛ ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ህወሓት እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም” ሲሉ ተናገሩ።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ የቀረበውን የክተት ጥሪ ተቀብለው በማይፀብሪ ግንባር ተሰልፈዋል።
“ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር ኢትዮጵያዊ ሁሉ መታገል አለበት” የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ “በግንባሩ እየተፋለምኩ ያለሁት የሀገሬን ሉዓላዊነት ለማስከበር ነው” ብለዋል፡፡
በተሰለፉበት ግንባር የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የጸጥታ ሃይሎችና የአካባቢው ሕዝብ በጠላት ላይ ድል እየተቀዳጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
መላው ሕዝብ በድል አድራጊነት መንፈስ ለሀገር ሉዓላዊነትና አንድነት በመዋደቅ ለግለሰቦች ስልጣን ሲል ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ቡድን በያለበት መታገል እንዳለበት አመልክተዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት “እኛ ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ቡድን ይፈርሳል እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ይህም በተግባር እየታየ ነው” ብለዋል።
አሸባሪው ህወሓት ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማት፣ ቤተ-እምነቶችን እና የሕዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶችን እያወደመና እየዘረፈ የሚገኘው አሸባሪው ቡድን የሚነዛውን የሐሰት ወሬ መከተል እንደማያስፈልግ አስገንዝበዋል።
“የኢትዮጵያ ሕዝብ ድል እያደረገ እንደሆነ መታወቅ አለበት” ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ÷ ሁሉም ዜጋ ባለው አቅም በግንባር በመገኘትና ደጀን በመሆን ለአገሩ ነፃነት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቡድኑ ምንም የማያውቁ ህፃናትን ለጦርነት እያሰለፈ ለሞት እየዳረጋቸው እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version