Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፍርድ ቤቱ በሀገር ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሴር ወንጀል የተከሰሱ 48 ግለሰቦች ላይ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ከአሸባሪው ህወሓት ጋር በማበር በሰራዊቱና ሀገር ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሴር ወንጀል በተከሰሱ የዕዙ አባላት ላይ የማጠቃለያ ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ተቀመጠ።
ተከሳሾቹ የሰራዊት አባላት በመንግስት ላይ እንዲያምጹ በማነሳሳትና አባላትን በማስኮብለል ጨምሮ ሀገር ላይ ጉዳት እንዲደርስ የተለያዩ ሴራዎችን በመጠንሰስ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናቸው ፡፡
ዛሬ ችሎት የተቀመጠው ፍርድ ቤቱ በ47 መዝገቦች የ48 ተከሳሾች ጉዳይ ላይ የማጠቃለያ ውሳኔ ለመስጠት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በተመሳሳይ ወንጀል በተከሰሱ አስር ግለሰቦች ላይ ከስምንት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version