Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ቤንች ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ነዋሪዎች ለሃገር መከላከያ ሰራዊት 32 ሰንጋዎችን እና ሌሎች ድጋፎችን አድርገዋል፡፡

የወረዳው ህዝብ በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው ሰራዊት ድጋፉን ሲለግስ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም በሶስተኛ ዙር 32 በሬ፣ 18 በግ ፣ 6 ፍየል እንዲሁም 14 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በወረዳው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም የወር ደመወዛቸውን 20በመቶ ለግሰዋል፡፡

በአጠቃላይ ከደቡብ ቤንች ወረዳ ከመጀመሪያ ዙር እስከ ሶስተኛ ዙር ከ3 ሚሊየን 750 ሺህ በላይ ግምት ያለው ድጋፍ መደረጉ ታውቋል፡፡

በአለማየሁ መቃሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version