Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ነገ የኢትዮጵያዊነት ቀን በመላ ሀገሪቱ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ነገ የኢትዮጵያዊነት ቀን በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ እንደሚውል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ አዘጋጅነት በመላው ሀገሪቱ ” ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ! እዘምራለሁ!” በሚል ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ በማሸብረቅ ፣ ሰንደቅ ዓለማውን በማውለብለብና ከፍ በማድረግ ከጠዋቱ 2 ከ 30 ላይ ለሁለት ደቂቃ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የሚደረግበት ዕለት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይህንን ቀን በያለበት ሆኖ በተጠቀሰው ሰዓት እንዲያከብር የከተማው አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version