Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ጎንደር ዞን ወደተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ገብቷል – አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ ገብቶ የተቀበረበት የደቡብ ጎንደር ዞን ወደ ተሟላ ሠላማዊ እንቀስቃሴ መመለሱን የዞኑ አስተዳዳሪ አስታወቁ፡፡
ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፥ ወራሪው የህወሓተ ቡድን የገባበት ደቡብ ጎንደር ዞን መቀበሪያው ሆኗል፡፡
በከባድ መሳሪያ ተኩስ ሲናጥ የሰነበተው ኅብረተሰቡ በአሁኑ ወቅት ሠላማዊ እንቅስቃሴውን በመቀጠል ተረጋግቶ ኑሮውን እየመራ ሠራዊቱንም እያገዘ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ህዝቡ ሠላማዊ ኑሮውን እንዲቀጥልና ወደ ሥራ እንዲገባ ለማስቻል ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ በወራሪው ጠላት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ እንደ መብራትና ቴሌ ያሉ መሠረተ ልማቶችም ወደ አገልግሎት እየገቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ እየተመለሱ መሆናቸውን፤ አመራሩም ወደ መደበኛ ሥራው መመለሱንና የተጠናከረ አደረጃጀት መፈጠሩን እንዲሁም የመንግስት መዋቅሮች ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም “ጠላትን ቀብረን እስከምነጨርሰው ድረስ ተረባርበን እናጠፈዋለን፡፡ ጠላትን ከቀበርንበትና ካስለቀቅንብትን ቦታ አልፈን መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ ጠላት እስከ መጨረሻው እናጠፋዋለን” ብለዋል፡፡
ለዚህም በየአካባቢው ያሉት አመራሮች እየተደገፉና እየተጠናከሩ ህዝቡን እንዲያነቁና እንዲያደረጁ እንዲሁም ለወታደራዊ ሥራው የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እንዲገኙ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people standing, military uniform and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version