Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊ ከታሊባን አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ አፍጋኒስተን ገብተዋል፡፡
ማርቲን ግሪፍትስ ወደ አፍጋኒስታን ቀኑት ከታሊባን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናግረዋል፡፡
በእስካሁኑ ቆይታቸውም ከታሊባኑ መሪ ሙላህ ባራዳር እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም በሀገሪቱ እርዳታ ለሚፈልጉ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ማርቲን ግሪፍትስ በሀገሪቱ የሰብዓዊ እርዳታ በተሳካ መልኩ እንዲሰራጭ ሁሉም ወገኖች አስተማማኝ ደህንነት እንዲኖር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
በተለይም ሴቶች፣ ህጻናት እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ልዩ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የታሊባን አመራሮች በበኩላቸው በሀገሪቱ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስፈላጊውን እገዛ እናደርጋለን ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version