Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ 108 ሺህ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ተጨማሪ 108 ሺህ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መረከቧን የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
 
ክትባቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተረክበዋል፡፡
 
የተበረከተው ክትባት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ክትባቱ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የኮሮና ቫረስ ክትባት ሂደት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version