Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት የ60 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሰባሰበውን 60 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቧል፡፡
ድጋፉን ያሰረከቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና÷ ድጋፉ አስተዳደራዊ ወጭዎችን በመቀነስ እና ከሰራተኞች በማሰባሰብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ድጋፍ ሀገር ሰላም ሆና የመማር ማስተማር ስራው እንዲቀጥል መከላከያን መደግፍ የሚገባ በመሆኑ ነው ሲሉ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀንአ ያደታ ዩኒቨርሲቲው ያደረገው ድጋፍ ትልቅ ከመሆኑም ባሻገር ዓላማውን ለመደገፍ የተነሳበት መንገድም አበረታች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ አስከአሁን ድረስ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 240 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተሰባስቧል ያሉት ዶ/ር ቀነአ ያደታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ግን ከሁሉም የላቀ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካደረገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የሕክምን ባለሞያዎችን ወደግምባር በማዝመት አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version