Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕላን ኢትዮጵያ በጂማ ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ችግረኞች የድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕላን ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የአዲስ አመት በአል ምክንያት በማድረግ በጅማ ዞን በነዲ ጊቤ ወረዳ ለችግር ለተጋለጡ 2 ሺህ 64 የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድርጅቱ ያደረገው ድጋፍ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት እንዳለው ተነግሯል።
የፕላን ኢትዮጵያ ጅማ ቅርንጫፍ ሃላፊ አቶ ከተማ ገመቹን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው ፥ ለ300 አቅመ ደካሞች የዱቄት፣ የዘይትና የሳሙና ድጋፍ ተደርጓል።
በተፈጥሮና በተለያዩ አደጋዎች የአካል ጉዳት ለገጠማቸው ወገኖችም 15 ክራንችና ሁለት ዊልቸር መለገሱን ሀላፊው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ለ1ሺህ 664 ችግረኛ ተማሪዎች የደብተር፣ የእስኪሪብቶና የእርሳስ ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version