Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የካማሽ ነዋሪዎች የትህነግ ተላላኪ በሆነው ታጣቂ ቡድን ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ነዋሪዎች በክልሉ በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ሃይል ላይ መንግስት የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ፡፡
ነዋሪዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡት በዞኑ ካማሽ ከተማ ዛሬ ባካሄዱት ሠላማዊ ሰልፍ ላይ ነው፡፡
በሰለማዊ ሰልፉ ላይ ጫካ ዉስጥ ያሉ የታጠቁ ቡድኖች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፣ የጉሙዝ ህዝብ የጁንታው ተላላኪ ሊሆን አይገባም፣ ወደ ጫካ የገቡ የጉሙዝ ተጣቂዎች ጉሙዝን አይወክሉም የሚሉ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡
የሽርተኛውን ህወሃት የጥፋት እቅድ ለማስፈጸም በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ሃይል በንጹሃን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት አውግዘው መንግስት በጥፋት ቡድኑ ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ባደረጉት ንግግረ በካማሽ ዞን የሽብር ቡድኑ ተላላኪ የጥፋት ኃይሎች በተዳጋጋሚ ጊዜ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በንፁኃን ዜጎች ላይ ኢ ሰብዓዊ ድርጊት መፈፀማቸውን ገልፀዋል፡፡
የካማሽ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ኩመራ በበኩላቸዉ ፀረ-ሰላም ቡድኑ በንፁኃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለዉ ሞትና ስቃይ ሊቆም ይገባል ብለዋል።
ወጣቶች የሽብር ቡድኑ ህወሃት ተላላኪ መሆን የለባቸውም ያሉት አቶ ታሪኩ አሁን በጫካ ዉስጥ ያሉ ተጣቂዎች እጃቸዉ በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጡም ጥሪ ማቅረባቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘገባ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version